• Mon - Sat 8.00 - 18.00
 • 1010 Moon ave, New York, NY US
 • +1 212-226-3126


ሁሉንም ያሽቶች አሳይ

የያሽት ግዥ

ያሽት መግዛት የመጀመሪያዎ ከሆነ እጅግ ከባድ ኃላፊነት እና ውስብስብ ሂደት ነው። አንድ ሰው በርካታ መስፈርቶችን በአንድ ጊዜ ማገናዘብ አለበት። ለአንዳንድ ሰዎች በጥቂት ቀናት ውሳኔ ላይ ይደርሳሉ፣ ሌሎች ደግሞ ምርጫቸውን ለመወሰን ወራት ሊያስፈልጋቸው ይችላል። የግዥ ውሳኔ በገንዘብ አቅርቦት ላይ ብቻ የሚወሰን አይደለም። አንድ ሰው የጀልባውን ጥራት እና ሁኔታ፣ የምርት እና ጥገና የጊዜ ማዕቀፍ እንዲሁም ተጨማሪ ሳይታዩ የቆዩ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ ማስገባት አለበት።

አዲስ ወይም ጥቅም ላይ የዋሉ ጀልባዎች?

የግል ያሽቶች እንደሚከተለው ይመደባሉ፦

 • በትዕዛዝ የተዘጋጁ
 •  ምርት
 • በከፊል በትዕዛዝ የተዘጋጁ
 • ከዚህ ቀደም ጥቅም ላይ የዋሉ

ውሳኔ በሚያሳልፉ ጊዜ፣ የጀልባውን ዋጋ እና የጥገና ፍላጎቱን ግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው። አዲስ እንደግል ፍላጎት የተበጁ ጀልባዎች በጣም ውድ ናቸው። ቢሆንም ቅሉ፣ ለደንበኛው በተለይ የተሰሩ እና እጅግ ዘመናዊ ናችው።

ድሕረ ገበያ ጥቅሞች እና ጉዳቶች

የመስመር ላይ የድሕረ ገበያ ግብይት ያሽቶች የግዥ ወጪዎችን በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳሉ። ነገር ግን፣ የድሕረ ገበያ ግዥ አንዱ ጉዳት ጀልባው በኦክሲዴሽን ሊጠቃ መቻሉ ነው። ያሽቶች ለውሃ የተጋለጡ በመሆናቸው፣ በጊዜ ሂደት የብረት ኦክሲዴሽን ወይም ዝገት ሊደርስባቸው ይችላል። በተጨማሪም ሻጋታ ሊፈጠር ይችላል። ስለሆነም፣ አንድ ባለቤት ዘወትር በጀልባው ላይ በዝገት እና ሻጋታ ምክንያት ሊፈጠሩ የሚችሉ እንከኖችን በዓይን በማየት መከታተል ያስፈልገዋል፤ ያ ካልሆነ ግን የጀልባውን ዕድሜ ያሳጥሩታል። ያም ሆኖ እያለ፣ በርካታ ባለቤቶች የጀልባቸው ጤና እና ጥገና ላይ ቁጥጥር ያደርጋሉ። ጠንቃቃ ባለቤት የመሪ አጠቃቀም እና የጥገና ምክሮችን ማቅረብ ይችላል።

በሞተር ኃይል መጓጓዝ ወይስ በነፋስ ኃይል

በያሽት መጓዝ ከጥልቅ ፍቅር ጋር ተወራራሽ ትርጉም ይዟል። ነገር ግን፣ ያ ምስል በጊዜ ሂደት ቀስ በቀስ እየደበዘዘ ነው። ምንም እንኳን ጀልባው ለቀዘፋ የማያስቸር ቢሆንም፣ ቀደም ብሎ ችሎታው እና እውቀቱ ከሌለ፣ እንዲህ አይነቱን ጀልባ መቅዘፍ አስቸጋሪ ይሆናል። በዚህም ምክንያት፣ በሞተር የሚሰራ ጀልባ ለቀዘፋ የበለጠ ቀላል እንዲሁም በልቅ ውሃ ላይም ፈጣን ነው። አንዱ ጉዳቱ የጥገና እና የክንውን ወጪዎቹ ከፍተኛ ናቸው።

የታለመለት ጥቅም

ያሽቶች፣ ጥቅም ላይ በሚውሉበት የውሃ አካባቢ መሰረት በ 4 ምድቦች ይከፈላሉ፦
• ውⷃኖሶች
• ባህሮች
• የዳርቻ አቅራቢያ ውሃዎች
• ሐይቆች

ከፍተኛ ልምድ ያካበትን ያሽት አቅራቢዎች እንደመሆናችን፣ አዲስ ቀዛፊዎች ምን አይነት የውሃ አካባቢን ለቀዘፋ እንደሚመርጡ እንዲወስኑ እንመክራለን። አንድ ሰው የሚወስደው የጉዞ አይነት፣ አጭር ጉዞዎችም ሆኑ ረጅም፣ ወይም ወደባህር ማዶ የሚደረጉ ጉዞዎች፣ በደንብ መጤን አለባቸው። አንዳንድ ሰዎች በላዩ ላይ መኖር የሚያስችል አዲስ ያሽት መግዛት ይፈልጋሉ። እንዲህ አይነት ውሳኔ ላይ የሚደርሱ ሰዎች የጀልባውን እርዝመት እና ወርድ፣ የመያዝ አቅም፣ እና አመቺነት ከግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

የትንንሾቹ ምድብ ውስጥ የሚመደቡ ያሽቶች፣ እርዝመታቸው ከ 6 ሜትር የማይበልጥ ሲሆን፣ ለአጭር ጊዜ ቆይታ የቡድን ጉዞዎች ተመራጭ ናቸው። እነኚህ አነስ ያሉ ጀልባዎች ለማጓጓዝ ቀላል በመሆናቸው ይመቻሉ። አርባ ጫማ እርዝመት ያለው ያሽት ተለቅ ላሉ ኩባንያዎች የበለጠ ተመራጭ ነው።

ያሽት መግዛት እና አትራፊነቱ

ጥሩ ያሽት ጥሩ ገንዘብ ያስወጣል እንዲያም ሆኖ፣ ውድ ያሽት መግዛት የሚከተሉትን ጥቅሞች ይሰጣል፦

 1. ጥሩ ኢንቨስትመንት ነው። ገንዘብን በአካውንት ውስጥ ወይም በቤት ውስጥ ማስቀመጥ በአብዛኛው አትራፊ አይደለም። ነገር ግን፣ ጥሩ ኢንቨስትመንት በዋጋ ግሽበእት ምክንያት የሚመጣን ጉዳት ለማለዘብ ይረዳል። የአንድ ጀልባ የቆይታ ጊዜ እሴት ከሞተር ተሽከርካሪዎች ይልቅ የረዘመ ነው። በመሆኑም፣ የያሽት ኢንቨስትመንቶች አስደሳች ናቸው።
 2. የዕረፍትና ሽርሽር ዕድሎች። በተጨማሪም፣ ያሽትን በባለቤትነት መያዝ ተጨማሪ የመዝናናት ዕድሎችን ያመጣሉ። በቀላሉ ለመግለጽ፣ አንድ ሰው በማንኛውም ጊዜ ወደ ባህር ለመሄድ ነጻነቱ ይኖረዋል።
 3. ጤናማ የሕይወት ዘይቤ። የያሽት ባለቤቶች ከባህር ጋር በመጫወት በርካታ ጊዜያቸውን በነፋሻ አየር ውስጥ ያሳልፋሉ፣ ይኽም ጤናን ለመጠበቅ ከመርዳቱም በላይ ጥሩ የአካል ብቃትን ያዳብራል። ከዚህም በተጨማሪ፣ የውሃ ጀልባ ባለቤት መሆን ትልቅ ኃላፊነት ነው። ያሽቶች ቅርብ ክትትል እና ጥገና ይፈልጋሉ። ባለቤቱ ሁልጊዜ ተቀምጬ እዝናናለሁ ብሎ ማሰብ የለበትም።
 4. ለጀልባ አድናቂዎች የክለብ አባልነት ሕይወትን ከባህር ውጭ ማሰብ የማይችሉ ሰእዎች አሉ። ሁሉም የያሽት ባለቤት የዚህ እንግዳ ተቀባይ ማኅበረሰብ አባል ይሆናል። የያሽት ባለቤቶች ወጣ ያሉ ስነ ባህሪዎች እና ለሕይወትም ልዩ ዕይታ አላቸው።
 5. ለግል ጠንካራ ድብርት ማስወገጃ በባህር ላይ በሚቀዝፉ ጊዜ፣ ችግርዎ በባህሩ ዳርቻ ይቀራሉ፣ ወይም ሟሙተው ይጠፋሉ። የያሽት ባለቤት በመሆን አንድ ሰው ይህንን ነጻነት በየቀኑ ያጣጥማል።

 

ጀልባዎን ሲመርጡ በደስታ እናግዝዎታለን። የሆነው ሆኖ፣ የድር ጣቢያችን መፈክር ማንም ሰው ያሽት መግዛት ይችላል ይላል።