Аренда (чартер) яхт по всему миру

available 0cars

ከፍተኛ ወጪ የሚያስወጡ በዓላትን ለማክበር አቅም ያላቸው ሰዎች ቁጥር ከእለት ወደ እለት እየጨመረ ነው። በአብዛኛው ከተለመደው በሪዞርት ውስጥ ከመዝናናት ይልቅ፣ በርካታ ሽርሽሮች በባህር ዳርሻ በምቹ ያሽቶች መንሸራሸርን ይመርጣሉ።

ከመካከላቸው ሃብታሞቹ የራሳቸውን ያሽቶች ይገዛሉ፣ እናም በቅንጡ ጀልባቸው የት እና ወደየት መጓዝ እንዳለባቸው ይወስናሉ። ሌሎቹ ደግሞ ትልቅ ግዥ ከመፈጸም ይልቅ ያሽት መከራየትን ይመርጣሉ። እንዲህም ሆኖ፣ ይህ ሁኔታ መጥፎ አይድለም፣ ምክንያቱም ቅንጡ የሆነ ምቾትን ለማግኘት ዕድሉን ይፈጥርላቸዋል። ስለሆነም በመጠነኛ ወጪ ጥሩ ጊዜ ማሳለፍ ይችላሉ።

ያሽት በቻርተር መከራየት ምን ያህል ይፈጃል?

ለያሽት የሚያስፈለውን የኪራይ ወጪ ከመመልከታችን በፊት፣ መጀመሪያ የያሽት ኪራይ ምን ምን እንደሚሸፍን እንመልከት።

ውድ እቃዎች

አንድ በአንድ እንመልከት፦

 1. 1. ትክክለኛ የያሽት ኪራይ ዋጋዎች፣ በመጀመሪያው ድርድር የተቀመጡም ይሁኑ ወይም በድር ጣቢያችን ላይ የሚታዩ፣ በካታሎጋችን ውስጥ ይገኛሉ። ዋጋው የሚከተሉትን ያካትታል
  – የያሽት ኪራይ
  – የኪራይ ረዳት
  – የተሳፋሪዎች አቅርቦት
  – የጀልባው እና የተሳፋሪዎች መድን
  – የማቆሚያ ክፍያ (moorgage)፣ በመንገዱ ላይ የሚያስፈልግ ከሆነ
  ዋጋው ብዙውን ጊዜ በጀልባው መጠን፣ በመዝናኛ አቅርቦቶቹ፣ በወቅቱ እና እድሜው ላይ ይወሰናል፣ ጀልባው አነስ ያለ እና እድሜው ከፍ ያለ ከሆነ፣ ኪራዩም ዝቅ ያለ ይሆናል። ቻርተር ለማድረግም ከወቅቱ ውጭ እና ቀድሞ በማስያዝ የሚደረገው ተመሳሳይ ነው ለሳምንታዊ የጀልባ ጉዞዎች መደበኛ ሳምንታዊ የያሽት ቻርተር ዋጋ አለ። አጭር የኪራይ ጊዜን ለማወቅ፣ ዋጋውን ለስድስት አካፍሎ ለሚከራይባቸው ሙሉ ቀናት ቁጥር ማካፈል ነው። ከአንድ ሳምንት በላይ ለሆኑ ጊዜዎች፣ ዋጋውን ለሰባት ማካፈል እና በሙሉ ቀኖች ቁጥር ማባዛት ነው። እንደዚሁም፣ የሙሉ ቀን ኪራይ በሁለቱም ሁኔታ ይለያያል። ለምን እንደዚህ ሆነ? የዋጋው ልዩነት የሚወሰነው ጀልባውን ለማዘጋጀት በሚያስፈልገው የሰው ኃይል ጋር ተመጣጣኝ በሆነ መጠን ነው። የጀልባው ሰራተኞች፣ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጉዞ የሚያደርጉት ዝግጅት ተመሳሳይ ነው። በተጨማሪም፣ የኪራይ ዋጋ በቻርተሮች መካከል የሚኖርን ከሥራ ውጭ የማቆሚያ ጊዜንም ያካትታል።2. ተያያዥ ወጪዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ
  – ነዳጅ
  – የተሳፋሪዎች አቅርቦት
  – የአልኮል እና አልኮል ያልሆኑ መጠጦች ለእንግዶች
  – ለመቁረጫዎች እና ለውሃ መሳሪያዎች ነዳጅ
  – የመተላለፊያ ክፍያ
  – የግል ማቆሚያ
  – ልብስ ማጠብ
  – የተሳፋሪዎች የግል ወጪዎች
  እነዚህ ወጪዎች በጉዞው ማብቂያ ላይ ይሰላሉ። በቀላሉ በመጀመሪያው ዋጋ ላይ የሰላሳ በመቶ ጭማሪ ማከል ይችላሉ።3. ቫት
  በርካታ የአውሮፓ ሕብረት አባል ሐገሮች የጭነት ቫት ሕግ አውጥተዋል። የቫት ወጪ በጉዞው በሚደረግበት ግዛትና ጀልባው በሚሸከመው ሰንደቅ ዓላማ ይወሰናል። በአማካይ፣ የቫት ወጪ በጭነቱ መጠን ላይ ከአስር እስከ ሃያ በመቶ ይጨምራል።4. የሰራተኞች ክፍያ።
  የእርስዎ የመዝናናት ተሞክሮ በጀልባው ላይ ባሉ ሰራተኞች ይወሰናል። ጀልባውን ይጠግናሉ እንዲሁም ያስሳሉ፣ እንዲሁም ለተሳፋሪዎች ሙሉ አገልግሎት ይሰጣሉ። በጀልባ ጉዞ ጊዜ፣ ለሃያ አራት ሰዓት በሥራ ላይ ይሆናል። ለዚህ ነው ጉርሻ መስጠት የተለመደ እና የሚጠበቅ ልማድ የሆነው። መድበኛ ጉርሻ በጣም ይለያያል። አውሮፓ ውስጥ ጉርሻ የኪራዩ ዋጋ ከአምስት እስከ አስር በመቶ ይሆናል። ጉርሻዎች በዩናይትድ ስቴትስ እና በካሪቢያን ይለያያሉ። አንድ ሰው በመደበኛው አገልግሎቶች ላይ ከአስር እስከ ሃያ በመቶ ማከል ይጠበቅበታል።5. ወደ መነሻ ወደብ መመለስ
  አንድ ሰው የራሱን ጀልባ እንዲሁም የሚሄድበትን መስመር መምረጥ ይችላል። አንድ ሰው ጀልባውን በማንኛውም ከኤምባርክተን የተለየ ቦታ መተው ከፈለገ፣ ወደ መነሻ ወደብ ለመመለስ ተጨማሪ ክፍያዎችን መጠበቅ አለበት። እነዚህ ወጪዎች አንድ ሰው ወደ መነሻ ወደቡ ቢመለስም ወይም ወደ ሌላ የመረጠው መዳረሻ ቢሄድ የነዳጅ ወጪዎችን ያካትታሉ።6. ተቀማጭ
  አብዛኛውን ጊዜ ተቀማጭ ማስያዝ አያስፈልግዎትም። ተቀማጮች የሚቀመጡት ለአስቸኳይ ጊዜ ወይም ለኮንትራት ማጠናቀቂያ ነው። የአዲስ ያሽት ባለቤቶች ሊከሰት ለሚችሉ ጉዳቶች የግዴታ ተቀማጭ ሊጠይቁ እንደሚችሉ መጠበቅ ይመከራል። እስከ 60 ሜትር ለሚረዝሙ ትልልቅ ያሽቶች ወጪው ከ 10,000 እስከ 20,000 ዩሮ ሊደርስ ይችላል። መነሻ የያሽት ወጪዎች አሉ።

የበጀት አማራጭ

ከፍተኛ ወጪዎችን የማይችሉ ከሆነ፣ ትንንሽ ጀልባዎች ከ15-20 ሜትር ርዝመት ያላቸው ተመራጭ ይሆናሉ። የትንንሽ ያሽቶች ዋጋዎች በአንጻራዊነት ትንሽ ነው። ለአንድ ሳምንት በአጠቃላይ ከ1500 እስከ 5000 ዩሮ ይሆናሉ። ትንንሽ ያሽቶች ትንሽ ሰራተኞችን ስለሚይዙ – አንድ ወይም ሁለት – ወጪዎቹም ከ 150 – 200 yuro በቀን ቢሆኑ ነው። በተጨማሪም፣ የምግብ ወጪዎች ለአንድ ሰው ከ200 -300 ዩሮ ይሆናሉ። ተጨማሪ ወጪዎች በአንድ ተሳፋሪ ከ50 – 100 ዩሮ ይሆናሉ።

ቅንጦት ብዙ ገንዘብ ይፈልጋል

ነገር ግን፣ ለእረፍት ሽርሽርዎ አቋራጮችን መጠቀም የማይፈልጉ ከሆነ፣ ረዘም ያለ ያሽት መከራየት ይችላሉ። እንዲህ ባለው ሁኔታ፣ በመዝናኛ ወቅት የሳምንት የቻርተር ዋጋ ከ 16000 ዩሮ ለ20 ሜትር እስከ 600,000 ዩሮ ለ 60 ሜትር ይደርሳል። በተጨማሪም፣ የሚታከሉ ተጨማሪ ወጪዎችን ይጠብቁ። መቶኛዎቻቸው ከላይ ተቀምጠዋል።

አሁን ሁሉንም የዋጋ አማራጮች ተመልክተናል፣ አሁን የያሽት መከራያ ጊዜ ነው

ScanMarine TM (Cofrance SARL) ከሁሉም የበለጠ ምርጫ ነው። ይህ ከፈረንሳይ ቁጥር አንድ የሪሲያ እና እንግሊዝ አለማቀፍ ደላላ ሲሆን ከፍተኛ የያሽት አቅርቦት አለው። አማራጮቹን ካታሎጋችንን በመመልከት መመልከት ይችላሉ። ቡድናችን የእረፍት ሽርሽር ተሞክሮዎን የበለጠ መልካም ለማድረግ፣ በእርስዎ የምቾት እና የመክፈል አቅም መጠን በጣም ምርጡን ያሽት እንዲመርጡ ይረዳዎታል፣